ቀበና ኪዳነ ምሕረት ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን

አሥራት

አሥራት ምንድነው?

ለመሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ አሥራት አለ?

የእግዚአብሔር ትዛዝ ነውን?

እግዚአብሔር አሥራትን ይቀበላልን? አሥራት መቼ ተጀመረ? የሚሉ አሉ፡፡

አንግዴህ ይህን የመሰሉትን ጥያቄዎች አጠቃለን ለመመለስ እንሞክራለን፡፡

በመሠረቱ እግዚአብሔር ከሚሰጠን በረከት፣ በምስጋና የምናቀርበው ምላሽ፣ አሥራት፣ መባ ወይም መስዋዕት ነው፡፡

ስለሆነም እግዚአብሔር ከሰጣቸው በረከት የመጀመርያ ምስጋና አቅራቢዎች በመጽሓፍ ቅዱስ እንደ ምንረዳው አቤልና ቃየን ናቸው፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 4፡ 2-6 እንመልከት፡-

አቤልም በግ ጠባቂ ነበር፤ ቃየንም ምድርን የሚያርስ ነበር፡፡ ከብዙ ቀን በኋላም ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ፤ አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስቡ አቀረበ፡፡

እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ ወደ ቃየንና ወደ መስዋዕቱ ግን አልተመለከተም፡፡

እዚህ ላይ ጠንቀቅ ብለን ነገሮችን እናስተውል፡፡ ስለ ቃየን ሲናገር፡-

ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር አቀረበ ይላል እንጂ ሌላ አይልም፡፡ ስለ አቤል ሲናገር ግን ከበጎቹ ብሎ ሳይደመድም ከበኵራትና ስብ በማለት የመስወዕቱን ጥራት ይነግረናል፡፡

በመቀጠልም ልብ እንበል አግዚአብሔር ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ 1 ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ አልተመለከተም ይለናል፡፡

እዚህ ላይ ፦ እግዚአብሔር በጥንቃቄ በትህትና የሚቀርብ መሥዋዕትን በርግጥም እንደሚቀበል ሲያመለክተን፣ ባንፃሩ ደግሞ በጥንቃቄ በትህትና የማይቀርበውን እነደሚጠላ ያሳውቀናል፡፡

በመቀጠልም አቤልንና መሥዋዕቱን ሲል አቤልን ተመለከተ የሚለው አነጋገር ከመሥዋዕቱ ቀድሞ እናገኘዋለን፤ ማለትም አቤልን ተቀበለው 1 በአበል ደስ አለው ሲል ሲያስረግጥልን ነው፡፡ አዎ አግዚአብሔር በቅንነት መልካሙን መርጦ ያለስስት በትሁትና የሚቀርብ መሥዋዕትን ሲቀበል፣ ከመስዋዕቱ አስቀድሞ በመስዋዕቱ አቅራቢው ደስ እንደሚለው ልናስተውል ይገባል፡፡

በአቤልና ቃየን ጊዜ መሥዋዕቱን የሚያሳርግ ካህን ባለመኖሩ መሥሣዕታቸውን በቀጥታ ሲያቀርቡ እናስተውላለን፡፡ ወደ ኋላ ግን የአሥራት ሥርዓት መኖሩን እናያለን፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 1- 17 ~ 2 እንመልከት፡

ኮሎዶጎምርንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ወግቶ ከተመለሰ በኋላም የሰዶም ንጉሥ የንጉሥ ሸለቆ በሆነ በሌዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ፡፡

የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ፤ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበር።

ባረከውም፡፡ አብራም ሰማይንና ምድርን ለሚገዛ ለልዑል እግዚአብሔር የተባረከ ነው፤ ጠላቶችህን በእጅህ የጣለልህ ልዑል እግዚአብሔርም የተባረከ ነው አለውም፡፡ አብራምም ከሁሉ አሥራትን ሰጠው፡፡

እንግዴህ በዚህ ጥቅስ እንደ ተመለከትነው የዕምነት አባት የሆነው ፡ በእግዚአብሔር የተመረጠው አብርሓም፤ የዕምነት ምሳሌ እንደመሆኑ ሁሉ፤ ለእግዚአብሔር ሊቀርብ የሚገባውን ለ እግዚአብሔር ካህን ለሆነው ለመልከጼዴቅ፣ አሥራት ማቅረቡን ተመልክተናል፡፡ በመሠረቱ ምሳሌነቱን በመከተል በተግባሩ ልንመስለው ይገባናል፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 28፣ 20 -22 እንመልከት፡-

ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፡፡ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን በምሄድበትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፤ የምበላውን እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፤ ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆነኛል፤ ለሓውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን እሰጣለሁ፡፡

ይህ ከሆነ ታድያ እግዚአብሔር አምላካችን አደለምን?

በሕይወት መንገድ እየጠበቀን በሰላም በልተን ፤ለብሰን የለምን አባታችን ሆይ ስንልስ ወደ እውነተኛው አባታችን አልተመለስንምን?

አብርሐምስ የእምነት ኣባታችን ኣደለምን?

ይሄስ ከሆነ እኛስ እግዚአብሔር ከሰጠን ሁሉ የምስጋና መሥዋዕት፣ መባ አሥራት ማቅረብ አይገባንምን?

ይሁን ይሄ በፈቃዳችን “ማድረግ ብንወድ ነው፤ ግን አባቱ ያከበረውን ልጅ ሊንቅ ይገባዋልን?

እግዚአብሔር የአብርሐም የይስሐቅ የያቆብ አምላክ ነኝ ሲል መጠሪያው ያደረጋቸውን አባቶች መከተል ተገቢ ኣይሆንምን?

ለነገሩ የአሥራትና መባ ነገር እንዲያው በቸልታ የሚቀር ሳይሆን በትእዛዝም እንዲህ ይለናል፡

ኣሪት ዘፀአት 34፡- 19 -25 እንመለከት ፡

ማኀፀንንም የሚከፍት ሁሉ የእኔ ነው፡፡ የከብትህም ተባት በኵር ሁሉ፤ በሬም ቢሆን በግም ሲሆን፤ የእኔ ነው፡፡ የአህያውንም በኵር በጠቦት ትዋጀዋለህ፤ ባትዋጀውም አንገቱን ትሰብረዋለህ፡፡የልጆችህን በኵር ሁሉ ትዋሻለህ፡፡ በፊቴም አንድ ሰው ባዶ እጁን አይታይ፡፡

ስድስት ቀን ትሠራለህ ፤ በሰባተኛውም ቀን ታርፋለህ፤ ... በአንተ ዘንድ ያለው ወንድ ሁሉ በእስራኤል አምላከ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት በዓመት ሦስት ጊዜ ይታይ፡

እዚህ ላይ በማጥ በቀጥታ አሥራት ባይልም፣ አሥራት ንበረትን፣ ጊዜና ጉልበትንም ማካተቱ ሊታወቅ ይገባል፡፡ በመቀጠል አሥራትን በሚገባ ሲጠቅስና ሲያዝ እንመለከታለን ! ነገር ግን፤ አሁንም ቢሆን መልእክቱን ብንመለከት፡-

· ስድስት ቀን ተመርቶ ሰባተኛው ቀን የኔ ነው ይለናል፡፡ ከአሥር አንድ ብቻ ሳይሆን፤ ከሰባት አንዱንም ይጠይቀናል፡፡ቀኖች ሁሉ የሱ የራሱ አይደሉምን? ቢፈቅድልን ስድስቱን ቀን ሰጠን እንጂ ጠቅላላውን ሲወስድስ ማን ይደው ነበር፤፤ የምድር ጌቶች ያለ እረፍት የሰው ልጅን በባርነት ቀንበር ከተው ሌት ተቀን ያሠሩበት ዘመን አልነበረምን?

እዚህ ላይ ግን እናስተውል ማንም ሰው ባዶ እጁን በፊቱ አይታይ ይላል፤ በመቀጠልም በዓመት ሦስት ጊዜ በፊቴ ይታይ ይላል፡፡

በዓመት ሦስት ጊዜ በፊቱ መቅረብ እንዳለብን 1 ባዶ እጅ መቅረብ እነደሌለብን ሲገልጽልን፤ ልብ እንበል፤ ቸግሮት አደለም፡፡ ሥርአቱን ሲያሳውቀን ነው፡፡ የሰማይ የምድር ንጉሥነቱን፤ አባትነቱን ሲገልጽልን ነው፡፡

በቤተክርስቲያን በሥርአተ ቅዳሴ ... መባችንና ቁርባናችንን ተቀበል፡፡ ›› እንላለን፡፡ መባ ሳናቀርብ ተቀበለን ማለት እንዴት ሊሆን ይችላል? መባችንን ተቀበል ለማለት ይብዛም ይነስም መስ ማቅረብ መስጠት ግድ ይለናል፡፡

አንዳንዴ መባ ተሰብስቦ በምክር ቤት ሲቀጠር እጅግ የቆሸሽ የተበጣጠሱ ብሮች መባ መቀበያ ውስጥ ተጥለው ይገኛሉ፡፡

አዎ ኪስ እንዳይቆሽሽ የተባሉ እነጂ የተሰጡ አይመስሉም፡፡ በርግጥ የብር ኣሮጌ የለውም ሁሉም ይሠራል፤ ማን አቤልንና ቃየንን እናስታውስ፡፡ አያየኝም ያው ነው በማለት መርጠን ያረጀውን በመስጠት መጣችንን አናርክሰው፡፡ አንድ ትልቅ ሰው የምናከብረው እጁን ቢዘረጋ የትኛውን እንሰው ይሆን?

ትንቢተ ሚልኪያስ 1፡- 6-9፡- እንመልከት

እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፤ ልጅ አባቱን፤ ባርያ ጌታውን ያከብራል፣ እኔስ አባት ከሆንኩ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታ ከሆነሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ዕውር መሥዋዕትንም ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? ያንን ለአለቃህ አቅርብ፣ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህን ይቀበላልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ እንጠንቀቅ፡፡

ትንቢተ ሚልኪያስ 1- 14 -- እንመልት

እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፤ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሰዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን፡፡ እንግዲህ እናስተውል ማሳነስም ሆነ፣ የማይገባ ነገር ለእግዚአብሔር ማቅረብ የተጠላ ነገር ነው፡፡

ኦሪት ዘለዋውያን 271 30 -34 - እንመልከት

የምድርም አሥራት 1 ወይም የምድር ዘር ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፤ የእግዚአብሔር ነው፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው፡፡ ሰውም አሥራቱን ሊበዥ ቢወድድ፤ አምስተኛ ይጨምርበታል፡፡ ከበሬም ሁሉ ከአሥር አንድ፤ ከአረኛውም በትር በታች ከሚያልፍ በግና ፍየል ሁሉ ከአሥር አንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፡፡ መልካም ወይም ክፉ እንዲሆን አይመርምር፣ አይለውጥም ቢለውጥም እርሱና ልዋጩ የተቀደሱ ይሆናሉ፣ አይብዡም፡፡

ምን እንበል ታድያ?? አሥራት መታዘዙ ግልጽ ሆኖ ይታያል 1 እንታዘዝ፣ አንታዘዝም ብለን ማን፣ አስራትን ጨርሶ ልናስቀር ቀርቶ፤ ባግባቡ ኣስራት ሳናስገባ ብንቀር፤ የእግዚአብሔር ቃል የሚለንን፣

በ ትንቢተ ሚለኪያ 38 እንመልከት

ሰው እገዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል፡፡ እናንተም የሰረቅንህ ምንድር ነው? ብላችኋል፡፡ በአሥራትና በበኵራት ነው፡፡

ኦሪት ዘኍልቁ 181 20- 24፡- እንመልከት

እግዚአብሔርም አሮንን ኣለው፡ በምድራቸው ርስት በመካከላቸውም ድርሻ አይሆንልህም፤ በእስራኤል ልጆች መካከል ድርሻና ርስትህ አኔ ነኝ፡፡ ለሌዊም ልጆች፤ እነሆ፤ በመገናኛ ድንኳን ኣገልግሎት ስለሚያገለግሉ፣ የእስራኤልን ልጆች አስራት ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ፡፡ከዚህም በኋላ ኃጢአትን እንዳይሸከሙ እንዳይሞቱም፤ የእስራኤል ልጆች ወደ መገናኛው ድንኳን አይቅረቡ፡፡ ሌዋውያን ግን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ይሥሩ፤ እነርሱም ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ ሰልጅ ልጃችሁ ለዘላለም ሥርዓት ይሆናል፤ በእስራኤል ልጆች መካከል ርስት አይወርሱም፡፡ ለእግዚአብሔር የማንሣት ቁርባን የሚያቆርቡትን የእስራኤልን ልጆች አሥራት ለሌዋውያን ርስት አድረጌ ሰጥቼአለሁ፤ ስለዚህ፡ በእሥራኤል ልጆች መካከል ርስት አይወርሱም አልኋቸው፡፡

ኦሪት ዘኁልቁ 18፤ 25 32፡- እንመልከት

ቁርባን የአሥራት አሥራት ታቀርባላችሁ፡፡ የማንሳት ቁርባናችሁም እንደ አውድማው እሀልና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ይቆጠርላችኋል፡፡ እንዲሁ እናንተ ደግሞ ከእስራኤል ልጆች ከምትቀበሉት ኢሥራት ሁሉ ለእግዚአብሔር የማንሣት ቁርባን ታቀርባላችሁ፤ የእግዚአብሔርን የማንሣት ቁርባን ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ፡፡ ከምትቀበሉት ስጦታ ሁሉ፤ ከተመረጠው ከተቀደሰውም ድርሻ ሁሉ፤ የእግዚአብሔርን የማንሳት ቁርባን ሁሉ ታቀርባላችሁ፡፡ ስለዚህ ትላቸዋለህ፡- ከእርሱ የተመረጠውን ባነሳችሁ ጊዜ አንደ አውድማው እሀልና እነደ ወይን መ ቀያው ፍሬ ለሌዋውያን ይቆጠራል፡፡ እናንተም ቤተሰቦቻችሁም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የማገልገላችሁ ዋጋ ነውና በሁሉ ስፍራ ትበላላችሁ፡፡ የተመረጠውንም ከእርሱ ባነሳችሁ ጊዜ ስለ እረሱ ኃጢአትን አትሸከሙም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤል ልጆች የቀደሱትን እታረክሱም፡፡

ወደ ዕብራውያን 7፤ 1-3፡- እንመልከት

የሳሌም ንጉስና የልዑል እግዚአብሔር ካህን የሆነ ይህ መልከ ጸዴቅ አብርሐም ነገስታቶችን ገድሎ ሲመለስ ከእርሱ ጋር ተገናኝቶ ባረከው፤ ለእረሱም ደግሞ አብርሐም ከሁሉ አሥራትን አካፈለው፡፡ የስሙም ትርጓሜ በመጀመሪያ የጽድቅ ንጉሥ ነው፤ ኋላም ደግሞ የሳሌም ንጉሥ ማለት የሰላም ንጉስ ነው፡፡ አባትና እናት የትውልድም ቁጥር የሉትም፤ ለዘመኑም ጥንት ለሕይወቱም ፍሜ የለውም፣ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል፡፡

በጥንቃቄ እናስተውል አባታችን አብርሃም ለሕይወቱ ፍጻሜ ለሌለው በእግዚአብሔር ልጅ ለተመሰለው ዘላለማዊ ካህን አሥራት ከፍልዋል፤ እኛም መክፈል ግድ ይለናል፡፡ ሚስጥሩ ታላቅ ነው፡፡ የጽድቅ የሰላም ንጉስ ነውና አብርሐም እነኳን አሥራት ሰጠ በሱም ተባረከ፡፡ እኛስ አሥራት መስጠት መባረክ አያስፈልገንምን?

ወደ ዕብራውያን 71 4 – 1- እንመልከት

የአባቶች አለቃ አብርሐም ከዘረፈው የሚሻለውን አሥራት የሰጠው ይህ ሰው እንዴት ትልቅ እንደነበር እሰኪ ተመልከቱ፡፡ ከለዊ ልጆችም ክህነትን የሚቀበሉት ከሕዝቡ ማለት ከወንድሞቻቸው፣ እነርሱ ምንም ከአብርሐም ወገብ ቢወጡ፤ ከእነርሱ አሥራትን በሕግ እንዲያስወጡ ትአዛዝ አላቸው፣ ትውልዱ ከእነርሱ የማይቆጠረው ግን ከአብርሐም አሥራትን አውጥቷል፣ የተስፋ ቃል የነበረውንም ባርኮአል፡፡ ትንሹም በታላቁ እንዲባረከ ከርከር የሌለበት ነገር ነው፡፡ በዚህስ የሚሞቱ ሰዎች አሥራትን ያስወጣሉ፤ በዚያ ግን የሚያስወጣ በሕይወት እንዲኖር የተመሰከረለት እርሱ ነው፡፡ ይህንም ለማለት ሊፈቀድ፣ አሥራትን የሚያስወጣ ሌዊ እንኳ በአብርሐም እጅ አሥራትን ሰጥቶአል፤ መልከ ጼዴቅ በተገናኘው ጊዜ ገና በአባቱ ወገብ ነበርና፡፡

በብሉይ ኪዳን አሥራት ምን ያህል ከባድ እነደሆነ ተመለክተናል፡፡ ቀድሞ ለነበሩ ካህናትም የታዘዘላቸው የማየሻር ነገር እነደሆነ የሚያከራከር ነገር አደለም፡፡ አሁን ደግሞ ወደ አዲስ ኪዳን መለስ ብለን አንመልከት፡፡ - « መልከ ጼዴቅ በ እግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል ይለናል ዕብራውያን 7፡3፡፡ እሱም አሥራት ተቀብልዋል፡፡

ዕብራውያን 71:11 እንመልከት

እርሱ ግን ፡ ጌታ ፡ አንተ እነደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ ማለ አይጸጸትም ብሎ በተናገረለት ከመሓላ ጋር ካህን ሆኖአልና ያለ መሐላ ካህን እንዳልሆነ መጠን፤ እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል፡፡

ብራውያን 7፤23-25

እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ እርሱ ግንለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ከህነት አለው፤ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለ ዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል፡፡

እዎን ይህ ካህን ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ነው፡፡ አግዚአብሔር አምላካችንም ስለ እርሱ የሚለንን ፡-

በሉቃስ ወንጌል 9135-36 እንመልከት

ከደመናውም :- የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ፡፡ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ፡፡

የዮሐንስ ወንጌል 25 -6 እንመልከት

የኢየሱስም እናት ለአገልጋዮቹ -- የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው:: እኛም ብዙ ጣጣ ሳናበዛ የሚለንን ብንሰማ ናደርግም ብንፈጽምም ይሻለናል፡፡

የዮሐንስ ወንጌል 5፣24 እንመልከት

ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም፡፡ አሺ እንግዴህ ከዚህ በመቀጠል የሚለንን እንስማ፡፡

የማቴዎስ ወንጌል ፡- 51 7-20 እንመለከት

እኔ ሕግንና ነብያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላቺሁ፤ ልፈጽመው እንጂ ለመሻር አልመጣሁም፡፡ እውነት እላቺኋለሁ፤ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፣ ከሕግ አንዲት ነውጣ ወይም አንዲት ነጥብ አታልፍም፤ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ፡፡ እንግዲህ ከነዚህ ሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ የገላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እረሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል፡፡

እዚህ ላይ ታድያ ምን እንጨምርበት ቁልጭ አድረጎ ነባሮን የለ፡፡ ባይሆን እነኳን እነዴት አንፈጽም በ ማን በኩል ብለን ብንጠይቅ ይሻል ይሆናል፡፡ እንግዲህ ሁሉን አዋቂ ዘላለማዊ ካህን የእግዚአብሔር ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመቀጠል መልስ ይሰጠናል አንዲህም ይለናል፡-

የማቴዎስ ወንጌል 1፤40-4 እንመልከት

እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፡፡ ልብ እንበል እናንተን የሚቀበል ይላል : እነ ማንን? ማንን ምንን ትቶልን ነው? አሁንም የሚለንን እንስማ፤

የማቴዎስ ወንጌል 1618-20 እንመልከት

እኔም እልሃለሁ፤ አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም፡፡ የመንግሥተ ሰማያትን መከፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል፡፡

ተነገረን እንግዴህ ጆሮ ያለው ይስማ ማለት ብቻ ነው፡፡ የገሃነም ደጆች የማይችልዋት፤ እናንተ የተባሉትስ ምን ይላሉ?

የቤተክርስቲያን ትዛዛት፡-

  1. በእሁድ ቀንና በታላቅ በዓል ቀን ቅዳሴ ስማ
  2. ባመቱ ኃጢአትህን ተናዘዝ
  3. በፋሲካ ወራት በሚገባ ቁረብ
  4. የታዘዘውን ጾም ሁሉ ጹም
  5. ለቤተከርስቲያን ከአሥር አንድ ስጥ
  6. ቤተከርስቲያን በከለከለችበት ጊዜ ሠርግ አታድርግ፡፡

የቤተክርስቲያን ትዛዛትን ሁሉንም መመልከታችን ጥሩ ነው ሆኖም ግን ቁጥር አምስትን መልሰን ብናየው፤ ለለዊ ዘሮች ለሌዋውያን ለእግዚአብሔር ካህናት የታዘዘውን አሥራት ከማረጋገጥ ሌላ ምን ይለናል?፡፡

እናስተውል --

አሥራት የመከፈል ጥቅሙ የማን ነው? ሊቃሉ የሚታዘዙትን ሕያው ያደርጋልና፤ አሥራት ለምን እንከፍላለን? ሌዋውያን 1959 እንዲህ ይለናል። የምድራችሁን መከር በሰበሰባችሁ ጊዜ የአርሻችሁን ድንበር ፈጽማችሁ አትጨዱ፤ የመከሩንም ቃርሚያ አትቃር፣ የወይንህንም ቃርሚያ አትቃርም፤ የወደቀውንም የወይንህን ፍራ አትሰብስብ ለድሆችና ለእንግዶች ተወው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፡፡ ይለናል ፤ አዎን ሁሉ የሱ ነው ቃሉን መፈጸም ጥቅሙ ለራሳችን ነው፡፡ ሰላምና ፍቅር ሊሰጠን ስለሚፈልግ ነው፡፡ በቅን ልቦና ደስ ብሎን የምንከፍለውን እሱ ያያል፣ የማርቆስ ወንጌል 2፤42 44 ... ብዙ ባለ ጠጎችም ብዙ ይጥሎ ነበር አንዲትም ድሀ መበለት መጥታ አንድ ሳንቲም የሚያህሉ ሁለት ናስ ጣለች፡፡ ደቀ መዝሙርቱንም ጠርቶ ፡- እውነት አላችኋለሁ በመዝገብ ውሰጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና! ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች አላቸው፡፡ « እንግዲህ እንመልከት፣ የሰጠችውን ሁሉ አብልጣ ሰጠች 1 ብሎን የለምን?

ገበሬ እግዚአብሔርን አምኖ የዘራው ቁና በብዙ እጥፍ ይመለስለት የለምን? ባይዘራው ያው ከያዘው ሌላ ምን ይተርፍ ነበር?

እንግዴህ እንዲባረክልን እንወቅበት፡፡፡

ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን

የሚለንን እንሰማ